ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የተመሰከረለት አመራር

መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከመጠበቅና ትምህርት ቤቶቻችንን ከመደገፍ ጎን ለጎን —ከቤት አቅርቦት ተመጣጣኝነት እስከ ህዝብ ደህንነት—ኬት ስቴዋርት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ።

ኬት ስቴዋርት ኖርዝ ቤተስዳን፣ ኬንሲንግተንን፣ ጋሬት ፓርክን፣ ሲልቨር ስፕሪንግን፣ ታኮማ ፓርክን እና የቼቪ ቼዝ ከፊል አካባቢዎችን የሚያካትተውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የዲስትሪክት 4 ምክር ቤት አባል በመሆን በኩራት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

እርሳቸው Government Operations and Fiscal Policy [የመንግስት ስራዎች እና የፊስካል ፖሊሲ] (GO) እንዲሁም ኦዲት ኮሚቴዎች ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ Transportation and Environment [በትራንስፖርት እና አካባቢ] (TE) ኮሚቴ ውስጥም አባል ናቸው። በዲሴምበር 2024 ዓ.ም ላይ በስራ ባልደረቦቻቸው በሰጡት ሙሉ ድምፅ ተመርጠው እስከ ዲሴምበር 2025 ዓ.ም ድረስ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።

ኬት 2025 ዓ.ም ላይ የሜትሮፖሊታን ዋሽንግተን መንግስታት ምክር ቤት ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት ሽልማት የሆነውን የኤልዛቤት እና ዴቪድ ስከል ሜትሮፖሊታን የህዝብ አገልግሎት ሽልማትን ተቀብለዋል። ይህንን ሽልማት ያገኙት በክልላዊ ትብብር በማድረገቻው፣ የክልሉን ደህንነት በማስጠበቃቸው  እና ለህዝብ አገልግሎት ባሳዩት ቁርጠኝነት ምክንያት እውቅና አግኝተዋል።  

በምክር ቤቱ ውስጥ ኬት እንደ የቤት አቅርቦት ተመጣጣኝነት፣ የኢኮኖሚ ልማት፣ የአእምሮ ጤና እና ለLGBTQ+ ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ባሉ ወሳኝ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም አመራር እየሰጡ ነው። ኬት ለማህበረሰባችን አስቸጋሪ ፈተናዎች ፈጣን እና ውጤታማ ምላሽ ይሰጣሉ።  የፌዴራል አስተዳደሩን ጎጂ እርምጃዎች እና በነዋሪዎች ላይ የሚያደርሱትን ቀጥተኛ ተጽእኖ በመገንዘብ፣ በፌዴራል በጀት ቅነሳ እና በኢኮኖሚ አለመረጋጋት ለተጎዱ ነዋሪዎች እርዳታ የሚሰጥ በአገልግሎት እና ድጋፍ የተባበሩ [United in Service and Support]የተሰኘ ተከታታይ መርሃ ግብር አስተዋውቀዋል።

እንደ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነታቸው፣ የትምህርት ቤቶቻችንን ፍላጎት የሚያሟላ፣ ለተቸገሩ ነዋሪዎች የሚውሉ የደህንነት መረብ አገልግሎቶችን በገንዘብ የሚደግፍ እና የካውንቲውን ግብር ሳይጨምር የ2026 በጀት እንዲጸድቅ አስችለዋል።

ኬት ዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አካባቢ የሚገኙ 24 ክልሎችን የሚወክሉ ከ300 በላይ የተመረጡ ባለስልጣናትን ባቀፈው የሜትሮፖሊታን መንግስታት ምክር ቤት [Board of the Metropolitan Council of Governments] (COG) ቦርድ ውስጥ ጭምር ያገለግላሉ።  ከ2022 እስከ 2023 የCOG ሰብሳቢ የነበሩት ኬት፣ ይህንን ሃላፊነታቸውን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ጥቅም ለማስከበር—ለምሳሌ ለቤት አልባነት ተግባራዊ እና ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማፈላለግ እና ለWMATA የረጅም ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ለማስገኘት—ይጠቀሙበታል።

በ2022 ወደ ካውንቲ ምክር ቤት ከመመረጣቸው በፊት፣ ኬት የታኮማ ፓርክ ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል። ለ30 ዓመታት ያህል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ የሆኑት ኬት እና ባለቤታቸው፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ምሩቃን የሆኑ የሁለት ልጆች ኩሩ ወላጆች ናቸው።